Logo

በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ

nomoto

ኢንተርፕራይዞች እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ

የሀገራችን ኢኮኖሚ ልማት ዓላማ ሁለተኛው ገጽታ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ከማረጋገጥ ባሻገር አንድ መሠረታዊ ዓላማ ተቀምጧል፡፡ ይህም ህዝቡ በየደረጃዉ ተጠቃሚ የሚሆንበት፤ አገራችን ከተመጽዋችነት የሚያላቅቅ ፈጣን ኢኮኖሚ ዕድገት በማረጋገጥ በሀገራችን የዳበረ የነጻ ገበያ ኢኮኖሚ ሥርዓት እንድኖር ማድረግ ነው፡፡

በሴክተሩ የሚከናወኑት ተግባራት የሀገራችንን  የኢኮኖሚ ልማት ዓላማ የተከተለ የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት የተቀመጡ ግቦችን ማሳካት እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ የኢንዱስትሪ ልማት በዋናነት  የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ማለትም የተለያዩ የማምረቻ ተቋሞችና ፋብሪካዎች የሚመረተዉን ማለታችን ስሆን በኢንዱስትሪ ልማት ዕቅዳችን ዉስጥ ወሳኝ ቦታ የተሰጠዉ  በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋሞች መሆኑ ነው፡፡ ይህ የሚሆነዉ በቅድሚያ የሥራ ዕድል የሚፈጠረዉ ዋናዉ ዘርፍ ይሄዉ በመሆኑና የኢኮኖሚ ልማት ዕቅዳችን አንድ መሠረታዊ ማጠንጠኛ የሥራ ዕድል መፍጠር በመሆኑ ነዉ፡፡

በክልላችን ያለዉን የሥራ አጥነት ችግር በመቅረፍና የወደፊት ኢንዱስትሪያልስቶችን በመፈልፈል ሰፊ መሠረት ያለዉ ባለሀብት በመፍጠር በከተሞች ልማታዊ ፖለቲካ በመገንባት ረገድ ወሳኝ ድርሻ የሚጫወተዉ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንቴርፕራይዞች ልማት ዘርፍ መሆኑን ተገንዝቦ መረባረብና የወጣቱን ሥራ ክህሎትና የሥራ ፈጣሪነት አመለካከት በማጎልበት የቁጠባ ባህሉን በማሻሻል ከዩኒቨርሲቲና ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋሞች የሚመረቁ ወጣቶችን ቅድሚያ በመስጠት በሥራ ዕድል ፈጠራ በሰፊዉ ወጣቶችን ማሰማራት ቀዳሚ ተግባራችን ነዉ፡፡ የኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ

ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፣

1)  የክልሉ ሥራ ፈላጊዎች በተለይም ወጣቶች እና ሴቶች በስራ ፈጠራ ላይ በስፋት እንዲሰማሩ ግንዛቤ ይፈጠራል፤ የስልጠና ድጋፍ፣ የመስሪያ ቦታ፣ ብድር፣ ገበያ ትስስር ምክርና ሌሎች ድጋፎች እንዲያገኙ ያደርጋል፤ ያመቻቻል፡፡

2)  ኢንተርፕራይዞች በማኑፋክቸሪንግ ሴክተር ተወዳዳሪ ሆነው ቀጣይነት ላለው ልማትና ለኢንዱስትሪ ልማት ጽኑ መሠረትን መጣል እንዲችሉ ድጋፍ የሚሰጡ ተቋማትን ያጠናከራል፤  ያደራጃል፡፡

3)  የኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪዎች የድጋፍ ፓኬጅ ያዘጋጃል፤ ያቀናጃል፤ ያስፈጽማል፤ በሥራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፡፡

4)  ለኢንተርፕራይዞች የስልጠና፣ የፋይናንስ አቅርቦት፣ የብደር፣ የማሽን፣ የገበያ ትስስር እና የተሟላ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡

5)  የስራ ፈጠራ እና የስራ ዕድል ላይ ጥናት ያደርጋል፣ ለሚመለከተው አካል  በማቅረብ ሲጸድቅ ሥራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፡፡

6)  ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪዎች ላይ ያሉ ምርጥ ተሞክሮዎችን በጥናት ለይቶ  በማቀናጀት እዲስፋፋ ያደርጋል፤ ተመሳሳይነት ያላቸውን ትስስር እንዲኖር ይሰራል፡፡

7)  ለኢንተርፕራይዝ ልማት የሚውሉ የክልሉ የተፈጥሮ ሀብት ላይ ከሚመለከተው አካል ጋር ጥናት ያካሂዳል፤ የጥናቱ  ውጤት ለሚመለተው አካል ያቀርባል፤ ሲጸድቅ በሥራ ላይ ያውላል፡፡

8)  የአንድ ማዕከላትን አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት ይዘረጋል፤ ያደራጃል፤ ያጠናከራል፡፡

9)  ኢንተርፕራይዞች የሚመዘገቡበትን፣ የሚደራጁበትን፣ ህጋዊ ሰውነት የሚያገኙበትን አሰራር ከሚመለከተው አካል ጋር ይሰራል፡፡

10) ኢንተርፕራይዞች የሂሳብ አያያዝ ምክርና የኦዲት አገለግሎት እንዲያገኙ ድጋፍ ያደርጋል፤ ሂሳባቸውን  ይመረምራል፤ እንዲመረመር ያደረጋል፤ በአፈጻጸማቸው እና ሀብት አያያዛቸው ላይ የኢንስፔክሽን ስራ ያካሂዳል፤ የእርምት እርምጃ ይወስዳል፡፡

11) የስራ ዕድል ፈጠራ ምክር ቤት በሁሉም ደረጃ  እንዲቋቋም ያደርጋል፤ የምክር ቤቱን ስራ ያደራጃል፤ አስፈላጊውን ድጋፍ ይሰጣል፡፡

General Information

Administrative Region
የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል
Organization Type
Gov
Sector
Services
Location
ሀዋሳ
Status