በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
1. የሴክተሩ አጠቃላይ ገጽታ
ትራንስፖርት ሴክተር የተለያዩ የአደረጃጀትና የአወቃቀር
ሂደቶችን ያለፈ ተቋም ሲሆን በተሻሻለው የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ኃላፊነት እንደገና
ለማደራጀት በወጣው አዋጅ ቁጥር 161/2008 የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ በስሩ ተጠሪነቱ ለቢሮው የሆነ የመንገዶች
ባለስልጣን ይዞ እንዲደራጅ ተደርጎ የትራንስፖርት ዘርፍና የመንገድ ዘርፍ ስራዎችን ቢሮው በበላይነት እንዲመራና እንዲያስተባብር
ስልጣን ተሰጥቶት ቆይቷል፡፡ ያም ሆኖ እያለ ግን ለአሰራር ባለመመቸቱ አሁንም በአዲስ መልክ የአስፈጻሚ አካላትን ለማደራጀት
እንደገና ተሻሽሎ በወጣው አዋጅ ቁጥር 174/2011 መሠረት የመንገዶች ባለስልጣን በተጠሪነቱ እንዲቀጥል በማጸደቅ የሁሉ አቀፍ ገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ፕሮግራም ከመንገዶች
ባለስልጣን ወደ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ እንዲደራጅ በማስወሰን ከሌሎች ዘርፎች ጋር በመቀናጀትና ሁሉ አቀፍ
ገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ፕሮግራም ዘርፍ በደቡብ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መስተዳደር ምክር ቤት በተሻሻለው የክልል
መንግስት የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 180/2012 አንቀጽ 17 መሠረት እንዲቋቋም በመደረጉ
ቢሮው አሽ/ተሽ/ብቃ/ማረ፣ መንገድ ትራ/ደህንነት ብቃ/ማረ፣ህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ብቃ/ማረ፣ የጭነት ትራ/አገ/ብቃት ማረ/ዳ
ይሬክቶሬቶችን፣ የሁሉ አቀፍ ገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ዘርፍና እንዲሁም
የዕቅድና በጀ/ዝግ/ክት/ግም፤ ግዢ ፋይናንስና ንብረት አስ/ር፣ የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር፣ የህዝብ ግንኙነት፣ የውስጥ ኦዲት፣
ዘርፌ ብዙ ምላሽና ማሳተባበር፣ ሥ/ፆታን በልማት ማካተትና ተጠቃ/ማረጋገጥ፣ ኢንፎርሜሸን ኮሙኒኬሸን ቴክኖሎጂ፣ ስነ-ምግባር መከታታያ፣
የሰው ሀብት መረጃ ስታትስቲክስና መረጃ ትንተናና ስርጭት የወል ዳይሬክቶሬቶችን በአደረጃጀት በማቀፍ የትራንስፖርትና የመንገድ ዘርፍ ሥራዎችን በበላይነት
በመምራትና በማስተባባር ላይ ይገኛል፡፡
በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
Organization Type | መንግስታዊ |
---|---|
Services | |
Location | ሀዋሳ |
Status | Active |
ContactUs
- ፌስቡክ
- +46 21 222 12