በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩል፣

1) የከተማ ልማትንና ኮንስትራክሽንን የሚመለከቱ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን፣ የልማት ፓኬጆችን እና ፕሮግራሞችን ይቅርጻል፣ ሲጸድቅምተግባራዊ ያደርጋል፣

2) የከተማ ነዋሪው ሕዝብ ከአቅሙ ጋር የተመጣጠነ መኖሪያ ቤት እንዲሰራ አጠቃላይ አቅጣጫ ለመቀየስ የሚያስችሉ ጥናቶችን ያካሂዳል፣ ለተግባራዊነታቸውም ለከተሞች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ይሰጣል፣

3) የከተሞችን የደረጃ መመዘኛና ደረጃ ይወስናል፣ ዕውቅና እንዲያገኙ ያደርጋል፣

4) ከተሞች የአካባቢያቸው የልማት ማዕከል እንዲሆኑ የተቀናጀ ድጋፍ ይሰጣል፣

5) የከተሞች ልማት ከገጠር ልማት እና ከድህነት ቅነሳ ጋር በተቀናጀ መንገድ የሚከናወንበትን ሁኔታ በሚመለከት ጥናት ያደርጋል፣ ተግባራዊ እንዲሆን ያግዛል፣ አፈጻፀሙን ይከታተላል፣

6) በከተሞች ዘመናዊ መሰረተ-ልማት እንዲስፋፋ ጥረት ያደርጋል፣ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል የለማ መሬት ያዘጋጃል፣

7) የክልሉን ከተሞች ፕላን ያዘጋጃል፣ አተገባበራቸውን ይከታተላል፣ድጋፍ ይሰጣል

8) በከተማ ፕላን ዝግጅት ለሚሰማሩ አማካሪዎች የብቃት ማረጋገጫ ይሰጣል፣ ደረጃቸውን ይወስናል፣ ፈቃድ ይሰጣል፣ ይሰርዛል፣

9) ከተሞች የሚያመነጯቸውን ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻዎች የሚወገድበትንና ውበት ያላቸው የመናፈሻ አገልግሎቶች የሚመሰረቱበትን የአሰራር ሥርዓት ይዘረጋል፣ድጋፍ ያደርጋል፣ 10)በከተሞች ለሕዝብ ልማት ሲባል ለመንግስታዊ ፕሮጀክቶችና ለሌሎች አገልግሎቶች ለሚዛወሩ ይዞታዎችና ከይዞታቸው ለሚፈናቀሉ ሰዎች ካሳ የሚከፈልበት ሥርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል አፈፃፀሙን ይከታተላል፣

11)ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የለማ መሬት ያዘጋጃል፣ ለተገልጋይ ያቀርባል፣ የአቅርቦቱን ፍትሐዊነት ያረጋግጣል፤ የተላለፈ መሬት ህጋዊነቱን ተከትሎ ለልማት መዋሉን ይከታተላል፣ ህገወጥ ግንባታዎችን ይቆጣጠራል ህጋዊ ሥርዓትን ያስይዛል፤

12)የመሬትና የንብረት ዋስትና ካሳ ሥርዓት ይዘረጋል፣

13)በቴክኖሎጂ የተደገፈና ወጥ የሆነ የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባና የአድራሻ መረጃ ሥርዓት በክልሉ ይዘረጋል፣

14)በከተሞች የልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ላይ ነዋሪው ህዝብ በተደራጀ አግባብ እንዲሳተፍ ለማስቻል የአሠራር ስርዓት ይዘረጋል፣ የማስፈጸም አቅምይገነባል፤ ያስተባብራል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣

15)የቤቶች ልማት ፕሮግራሞችን ይመራል፣ የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል የከተማ ነዋሪ ሕዝብ ከአቅሙ ጋር የተመጣጠነ የመኖሪያ ቤት እንዲሰራ ስልት ይቀይሳል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፣

16)የኮንስትራክሽን ዘርፉን በአግባቡ ለመምራት የሚያስችል የረጅም ጊዜ ስትራቴጂ ይነድፋል፣ ይተገብራል፤ ለዘርፉ ዕድገት አስፈላጊ የሆኑ ጥናቶችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ቅንጅት በመፍጠር ይተገብራል፤

17)በክልል ደረጃ የተወዳዳሪነት ብቃት ያለው የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ለመገንባት የሚያስችሉ የተመቻቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ያደርጋል፤ በዲዛይን፣ በጨረታና፣ በኮንትራት ይዘት ላይ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለበት ሥርዓት ይዘረጋል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤

18)በኮንስትራክሽ ሥራዎች ላይ ተገቢውን ቁጥጥር ያደርጋል፤ የኮንስትራክሽን ሥራዎችን ደረጃ ያወጣል፣ መከበራቸውን ይከታተላል፤

19)በክልሉ መንግሥት በጀት ለሚሠሩ ሕንፃዎች ዲዛይኖችና የግንባታውሎች እንዲዘጋጁ ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል፣ የግንባታ ሥራዎችን ይቆጣጠራል

20)የሕንፃ ኮድና ስታንዳርዶች በከተሞች ተፈጻሚ እንዲሆኑ ተገቢው አደረጃጀት፣ አሠራርና የሰው ሃይል አቅም እንዲፈጠር ድጋፍ ያደርጋል፤

21)በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚሰማሩ ባለሞያዎችን ይመዘግባል፣ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፤ የሥራ ተቋራጮችና አማካሪዎች የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፤

22)ዓላማውን ለማስፈጸም የሚችሉ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፡፡

በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ
Organization Type መንግስታዊ
Economy
Location ሀዋሳ
Status Active
ContactUs