በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የቴክኒክና ሙያ ት/ስልጠና ቢሮ

ቢሮው አጠቃላይ ገጽታ

የደቡብ ብሔር ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግሥት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ ዕድገት

በክልላችን 1987 . በፊት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና በተደራጀ መልኩ በመንግስት የሚተዳደር አልነበረም ሆኖም -

1.   በሀዋሳ ከተማ በስዊዱኖች የተሰራ ተግባር-ዕድ ተብሎ የሚጠራው

2.   ዲላ በካቶሊክ ሚሲዮኖች የተሰራ ዲላ ዶምቦስኮ ተግባር-ዕድ ተብሎ የሚጠራው

3.   አርባምንጭ ላይ የሚገኘው ተግባር-ዕድ በኖርጂያንስ ድርጅቶች የተቋቋሙ ሲሆን እነዚህ ተቋማት አሁንም ስልጠና በመስጠጥ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከነዚህ ሶስት መንግስታዊ ባልሆኑ የሃማኖት ድርጅቶች ከተቋቋሙት በቀር ሌላ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት አልነበረም፡፡

 1987 . የክልሉ ምክር ቤት በራሱ /ቤት አሰሪነት እያንዳንዳቸው 4 ጣሪያና ግድግዳቸው ቆርቆሮ የሆኑ ወርክ ሾፖችና በብሎኬት የተሰሩ 4 መማሪያ ክፍሎችና አነስተኛ የአስተዳደር ህንፃ ያላቸውን 7 የቴ// ተቋማት ገንብቶ የክልሉ ትምህርት ቢሮ እንዲያስተዳድር ተደርጓል፡፡

አነዚህ ተቋማት  

  • በጌዲኦ ዞን ዲላ ከተማ የዲላ /// ኮሌጅ
  • በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሀዋሳ ፖሊ /// ኮሌጅ (ከተግበረ-ዕድ ሌላ)
  • በወላይታ ዞን ሶዶ ፖሊ /// ኮሌጅ

ራዕይ

በክልሉ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት አስተዋጽኦ የሚያበረክት ብቁና በሙያው የሚተማመን ዜጋ በማፍራት የሕዝቡን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻልና ቀጣይነት ባለዉ ሁኔታ ከክልሉ ብሎም ከአገራችን ድህነትን ማጥፋት ነው፡

ተልዕኮ

በተለማጭና ውጤት ተኮር የትምህርትና ሥልጠና ሥርዓት በተለያዩ ደረጃዎች የትምህርትና ሥልጠናዎችን ለመስጠት እና ቴክኖሎጂዎችን በማሸጋገር ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እሴት የሚጨምሩ፣በዓለም አቀፍ ደረጃ በብቃት ተወዳዳሪ መሆን የቻሉ እስከ መካከለኛው ደረጃ የሰለጠኑ ዜጐችን ማፍራት ነው፡፡