በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

አመሰራረት

ይህ ተቋም ከ 1985  አስከ 1987 ዓ.ም የደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት የማስታወቂያ ቢሮ፤ ከ1987 አስከ1990 ዓ.ም የደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት የባህልና ማስታወቂያ ቢሮ ከ 1990 እስከ 1994 ዓ.ም የደቡብ፤ ብሄር፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት ማስታወቂያ ቢሮ፣ ከ1994 እስከ 1996 ዓ.ም የማስታወቂያና ባህል ቢሮ፣ ከ1996 እስከ 2002 ዓ.ም የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ፣ ከ2002 እስከ 2008ዓ.ም የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት፣ 2008 እስከ 2011ዓ.ም ፕሬስ ሰክሬታሪያት፣ ከጥቅምት 2012 ዓ.ም ጀምሮ በአዋጅ ቁጥር 180/2012 መሰረት የደቡብ ብሄር፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች  ቢሮ ሆኖ እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡

የደቡብ ብሄሮች፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ሴክተር አላማ ወቅታዊና ተአማኒ የመንግስት መረጃዎችን ለህብረተሰቡ በማድረስ እንዲሁም ህብረተሰቡ በመንግስት ፖሊሲዎች፤ ፕሮግራሞች፤ ፕሮጀክቶች፤ እቅዶችና አጀንዳዎች ላይ ያለውን እምነት፤ አቋም እና ዝንባሌ ለመንግስት በማደረስ በመንግስትና በህዝቡ መካከል ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር የክልሉን የልማትና ዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ እውን እንዲሆን በማገዝ የክልሉ ሠላም እንዲረጋገጥ እና ህዝቡ የደስታና የብልጽግና ህይወት እንዲጎናጸፉ ማስቻል ነው፡፡

የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኑኬሽን ጉዳዮች ሴክተርየደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ከተመሰረተበት ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ በተለያየ ስያሜ እየተጠራ አደረጃጀቱንም እየለዋወጠ ቆይቶ አሁን በቅርቡ ደግሞከጥቅምት 2012 ዓ.ም ጀምሮ በአዋጅ ቁጥር 180/2012 መሰረት የደቡብ ብሄር፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች  ቢሮ ሆኖ ተደራጅቷል፡፡

ይሁን እንጂ የተቋሙ ስያሜና አደረጃጀት በተደጋጋሚ ሲቀያየር የነበር ቢሆንም ከክልሉ መንግስት የተሰጡትን ኃላፊነቶች ለመወጣት የሚያስችሉትን ስትራቴጅዎችበመንደፍ ላለፉት ሁለት የስተራቴጂክ እቅድ ዘመናት እቅዶችን በማዘጋጀትእንዲሁም  የአደረጃጀትና የአሰራር ስርዓትን በመዘርጋት ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ህብረተሰቡን በየደረጃው ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራት ሲከናወኑ ቆይተዋል፡፡ 

በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
Organization Type መንግስታዊ
Services
Location ሀዋሳ
Status Active

የስራ ማስታወቂያዎች