በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ
የቢሮው ዳራዊ መረጃ
አመሰራረትና አደረጃት
በ1983 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ በተደረገው የመንግስት ለውጥና በ1985 ዓ.ም በተካሄደው የክልል መንግስት ምስረታ እንዲሁም የነበረው የማዕከላዊ መንግስት አስተዳደር ተለውጦ ሀገሪቱ ፌዴራላዊ የመንግስት አስተዳደር እንድትከተል መወሰኑን ተከትሎ ክልሎች ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ በመደረጉ ቢሮው በአዋጅ ቁጥር 7/1984 መሠረት ቀደም ሲል ከነበረው አደረጃጀት የተፈጥሮ ሀብት የሥራ ዘርፍ ራሱን ችሎ በቢሮ ደረጃ የተቋቋመ ሲሆን የግብርና ቢሮም የኅብረት ሥራን፣ የግብርና ግብዓትና ሌሎች ቀሪ የሥራ ዘርፎችን በመያዝ በቢሮ ደረጃ እንዲቀጥል ተደርጓል፡፡ ሕዳር 15/1988 ዓ/ም የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/ መንግሥት የአስፈፃሚ መ/ቤቶችን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን ባወጣው ዓዋጅ መሠረት ቀደም ሲል ለየብቻ ተደራጅተው የነበሩት የግብርና፣ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና የቡናና ሻይ ልማት ቢሮዎች በአዋጅ ቁጥር 03/1988 ተዋህደው የግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ተብለው ሲደራጁ ከነሐሴ 1989 ዓ.ም ጀምሮ በአዋጅ ቁጥር 14/1989 የኅብረት ሥራ ለብቻው በጽ/ቤት ደረጃ እንዲቋቋም ተደረገ፡፡
የግብርናና ገጠር ልማት ቢሮም በአዋጅ የተሰጡትን ሥራዎች አካትቶ በሁለት መምሪያዎች ተዋቅሮ እስከ 1994 ዓ.ም ሲንቀሳቀስ የቆየ ቢሆንም በሀገር አቀፍ ደረጃ ገጠርንና ግብርናን ማዕከል ያደረገ የልማት ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን በሥራ ለመተርጎም በሚደረገው ርብርብ የተለያዩ ተቋማትን በቅንጅት መምራት፣ የሰው ጉልበት፣ ሀብትና ጊዜን በመቆጠብ ቀልጣፋ አሠራርን መከተል እንዲያስችል ከሞላ ጎደል ተቀራራቢና ተደጋጋፊ እንዲሁም ተመሳሳይ የገጠር ልማት ራዕይ ያላቸውን መ/ቤቶች በአንድ ላይ አስተሳስሮ ለመምራት ሲባል የተደረገው የአደረጃጀት ለውጥ መሠረት በማድረግና በክልሉ ተጨባጭ ሁኔታ ላይ በማተኮር በገጠር ልማት ዙሪያ ተግባራዊ የልማት እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የሚገኙትን የክልሉ ተቋማት (ቢሮዎችንና ጽ/ቤቶችን) አቀናጅቶ በመምራት ቀልጣፋና ፈጣን ዕድገት በማስመዝገብ የገጠሩን ሕዝብ ብሎም አጠቃላይ የክልሉን ሕዝብ ኑሮ ለማሻሻል፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ሁለንተናዊ ዕድገት ለማስመዝገብ የደቡብ ክልል ገጠር ልማት ማስተባበሪያ ቢሮ በ1994 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር 36/1994 ተቋቋመ፡፡
በመቀጠልም በሀገራችን የተከሰተውን የለውጥ ፕሮግራም ተከትሎ ሁለቱ ቢሮዎች በክልሉ የገጠር ልማት ክላስተር ስር የግብርና ቢሮ በሚል ስያሜ በአንድ አደረጃጀት ተዋህደው በአንድ ቢሮነት እንዲሰሩ የክልሉ መንግስት የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን ባወጣው አዋጅ ቁጥር---/2014 መደንገጉን ተከትሎ የክልሉ ግብርና ቢሮ በስሩ የእርሻ ዘርፍን፣ የተፈጥሮ ሀብት ዘርፍን፣የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያና መኖ ልማት ዘርፍን፣ የእንስሳት ጤናና ግብዓት አቅርቦት ዘርፍን፣የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩትን፣ የግብርና ግብዓት አቅርቦት ዘርፍን፣ የአስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍን እንዲሁም የህብረት ስራ ኤጀንሲን፣ የአደጋ ስጋት ስራ አመራርና ምግብ ዋስትና ኮሚሽንን፣ የግብዓት ጥራት ቁጥጥርና ኳራንቲን ባለስልጣንን፣ የቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣንን እንዲሁም የድጋፍ ሰጪ ዳይሬክቶሬቶችና የስራ ሂደቶችን በክልል፣ በልዩ ወረዳ፣ በወረዳ፣ በቀበሌያትና በከተማ አስተዳደሮች መምሪያዎች፣ ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶችና ጽ/ቤቶች በማደራጀት ተልዕኮውን በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡
ተልዕኮና ራዕይ
ተልዕኮ (Mission)
የተፈጥሮ ሀብትን በመጠበቅና በማልማት፣ ሥነ-ምህዳርን መሠረት ባደረገ መልኩ የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀምና የልማት አውታሮችን በመዘርጋትና የተጠናከረ የግብርና ኤክስቴሽን አገልግሎት በመስጠት፣ በገበያ ተወዳዳሪ የሆነ ምርት በማምረትትና ምርታማነትን በማሳደግ የኅብረተሰቡን ገቢ ማሳደግ፡፡
ራዕይ (Vision)
በ2022 የተሸጋገረ ግብርና በመፍጠር በውስጣዊ ሸግግር ግብርናን ምርታማና ተወዳዳሪ በማድረግ የአርሶና አርብቶ አደሩን ገቢ ማሳደግና ከድህነት ማላቀቅ፣ ለሀጋራዊ ኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ደግሞ ሀገራዊ የምግብና ሥርዓተ-ምግብ ፍላጎት ያሟላ፣ ለኢንዱስትሪ ግብዓትና ለወጪ ንግድ በቂ ምርት ያቀረበና ወደ ዕሴት ጭመራ የተራመደ እና በገጠር በቂ የሥራ ዕድል የፈጠረ ዘረፍ ማድረግ!
በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ
Organization Type | መንግስታዊ |
---|---|
Services | |
Location | ሀዋሳ |
Status | Active |