...

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት

ደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ት ትንሿ ኢትዮጵያ

ዜናዎች

በጤና ዘርፍ የሚከናወኑ የግል ኢንቨስትመንቶች የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ከማድረግ ባለፈ ዘመኑ የደረሰበትን የሕክምና ቴክኖሎጂ ዕውን ለማድረግ የጎላ ሚና እንዳላቸው ተገለፀ፡፡
  • የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት
ጥር 13/2015
በጤና ዘርፍ የሚከናወኑ የግል ኢንቨስትመንቶች የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ከማድረግ ባለፈ ዘመኑ የደረሰበትን የሕክምና ቴክኖሎጂ ዕውን ለማድረግ የጎላ ሚና እንዳላቸው ተገለፀ፡፡ 
በከምባታ ጠምባሮ ዞን ቃጫቢራ ወረዳ ምስራቅ ሌሾ ቀበሌ ከአርባ ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለሚገነባው ዶ/ር ተሾመ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የመሠረት ድንጋይ ተጥሏል። 
በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ክልል የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ባዩሽ ተስፋዬ እንደገለፁት በጤናው ዘርፍ የሚደረግ የግል ኢንቨስትመንት በሕክምናው ዘርፍ ዘመኑ የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለኅብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል። 
Read More...
የባህል ስፖርቶችና ፌስቲቫሎች የሀገርን ሁለንተናዊ ገጽታ በማሳየት ለቱዝምና ኢንቨስትመንት ዕድገት ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተገለጸ፡፡
  • የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት
ጥር 14/2015 ዓ/ም
የባህል ስፖርቶችና ፌስቲቫሎች የሀገርን ሁለንተናዊ ገጽታ በማሳየት ለቱዝምና ኢንቨስትመንት ዕድገት ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተገለጸ፡፡
የደቡብ ክልል 20ኛ የባህል ስፖርቶች ውድድርና 16ኛ የባህል ፌስቲቫል በዲላ ከተማ በይፋ ተጀምሯል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ የኢፌዲሪ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነትን ጨምሮ የክልል፣ የዞንና ልዩ ወረዳዎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የስፖርት ልዑካን ቡድኖችና የባህል አምባሳደሮች ተገኝተዋል፡፡
በመክፈቻ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የዕለቱ የክብር እንግዳ የኢፌዲሪ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነትን እንደገለጹት የባህል ስፖርቶችና ፌስቲቫሎች የሀገርን ሁለንተናዊ ገጽታ በማሳየት ለቱዝምና ኢንቨስትመንት ዕድገት ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ፡፡
ሚኒስቴር መ/ቤታቸው ንቁ፣ ተወዳዳሪናና አሸናፊ ዜጎችን የመፍጠር ተልዕኮውን ለማሳካት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የተናገሩት አምባሳደር መስፍን ለዚህም የባህል ስፖርቶችን እነደዋነኛ መሳሪያ እንደሚጠቀም ጠቁመዋል፡፡
Read More...
በሀድያ ዞን ሆሳዕና ከተማ ባለ 3 እና 2 ሁለት እግር ተሽከርካሪዎች መገጣጠሚያ ፋብሪካ የሆነው ሆሳዕና የሞተር ተሽከርካሪዎች መፈብረኪያ እንዲስትሪ ተሽከርካሪዎችን በማምረት ለከተማውና ዙሪያ አካባቢ ህብረተሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበ እንደሚገኝ ገለፀ።
  • የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት
ታህሳስ 26/2015
በሀድያ ዞን ሆሳዕና ከተማ ባለ 3 እና 2 ሁለት እግር ተሽከርካሪዎች መገጣጠሚያ ፋብሪካ  የሆነው ሆሳዕና የሞተር ተሽከርካሪዎች መፈብረኪያ እንዲስትሪ ተሽከርካሪዎችን በማምረት ለከተማውና ዙሪያ አካባቢ ህብረተሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበ እንደሚገኝ ገለፀ።
መገጣጠሚያ ፋብሪካው ከ 2 መቶ ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ ወደ ስራ በመግባት በማኑፋክቸሪንግ ኢንዲስትሪ ዘርፍ የቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎት ሽግግርን በማስፋት ለዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር   እንደቻለ የተጠቆመ ሲሆን
የመፈብረኪያ ኢንዲስትሪው የስራ እንቅስቃሴን የዞኑና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በጋራ በመሆን ጎብኝተዋል።
Read More...
ሴራችን ሁሉን አቀፍ ማንነታችን አብሮ የመኖር የአንድነት ማሳያ ድንቅ ባህላችን" በሚል መሪ ቃል ማጠቃለያ ሴራ በዓል (መንገሰ) በሀላባ ዞን በዌራ ዲጆ ወረዳ በተለያዩ ባህዊ ትዕሪቶች ተከበረ
  • የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት
ጥር 4/2015 
ሴራችን ሁሉን አቀፍ ማንነታችን አብሮ የመኖር የአንድነት ማሳያ ድንቅ ባህላችን" በሚል መሪ ቃል ማጠቃለያ ሴራ በዓል (መንገሰ) በሀላባ ዞን በዌራ ዲጆ ወረዳ በተለያዩ ባህዊ ትዕሪቶች ተከበረ 
======
 በሀላባ ዞን በዌራ ዲጆ ወረዳ ሀላባ ሴራ በዓል (መንገሰ) በተለያዩ ባህዊ ትዕሪቶች በድንቃት ተከብረዋል።
በበዓሉ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዌራ ዲጆ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ጀማል ኢብራሂም የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸው አስተላልፈዋል።
Read More...
በእዣ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ጽ/ቤት የሳይንስ ሳምንት ተከብሮ ዋለ:
  • የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ
ጥር10/5/2015ዓም በእዣ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ጽ/ቤት የሳይንስ ሳምንት ተከብሮ ዋለ:
"የሳይንስናቴክኖሎጂ ክበባትን መደገፍ ለትውልድ ተስፋን መመገብ ነው በሚል መሪ ቃል"የሳይንስ ሳምንት ተከብሮ መዋሉን የእዣ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ሀላፊየሆኑት ወ/ሪት ረሂማ ሙህታጅ ገልጸዋል።
Read More...
"በየወቅቱ የዘመነ ቴክኖሎጂ መጠቀም ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለተቋማት ለማዳረስ ቁልፍ ሚና ይጫወታል"
  • የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ
ጥር 8/2015
"በየወቅቱ የዘመነ ቴክኖሎጂ መጠቀም ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለተቋማት ለማዳረስ ቁልፍ ሚና ይጫወታል" :- አቶ ዘላለም ጳውሎስ የወላይታ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪየ ኃላፊ
መምሪያውም ለሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ባለሙያዎች ለአምስት የሚቆይ የተግባር ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡
Read More...
በጌዴኦ ዞን ሳይንስ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት ስልጠና እየተሰጠ ነው
  • የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ
በጌዴኦ ዞን ሳይንስ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት ስልጠና እየተሰጠ ነው
ዲላ፡ጥር፣12/2015የጌዴኦ ዞን ሳይንስ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ከዞኑ ትምህርት መምሪያ ጋር በመሆን በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ለባለድርሻ አካላት የአቅም ግንባታ ስልጠና በዲላ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል።
በስልጠናው የሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር  ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች፣የመምህራን ልማት ባለሙያዎች፣የ2ኛ ደረጃ 
Read More...
የሳኢቴ ቢሮ በጥናትና ምርምር የተለዩና የተፈተሹ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን ናሙና በማምረት ለሚመለከታቸው አካላት አሸጋገረ፡፡
  • የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ
የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በጥናትና ምርምር የተለዩና  የተፈተሹ  ችግር  ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን ናሙና በማምረት ለሚመለከታቸው አካላት አሸጋገረ፡፡ 
የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በጥናትና ምርምር ያሰራቸውንና በተግባር የተፈተሹ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎች ናሙና በማስፋት ተጠቃሚው ማህበረሰብ ጋር እንዲደርሱ የሚያስችል ሰነድ በማዘጋጀትና በመፈራረም ከባለድርሻ አካላት ጋር በቀን 02/05/2015ዓ.ም 
Read More...
በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ትምህርት ቢሮ አዘጋጅነት የንባብ ዘመቻ አፈጻጸም ግምገማ በሳጃ ከተማ ተጀመረ ።
  • በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ
ጥር 13 /2015 ዓ/ም
በመድረኩ የየም ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ገ/ሚካኤል የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ህብረተሰቡን በማሳተፍ ለትምህርት ስራ አስፈላጊ ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረው በቀጣይም ይህ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል፡፡ ዋና አስተዳዳሪው አክለውም ልዩ ወረዳው ለቱሪስት መስህብ ምቹ ሁኔታ እንዳለው ገልጸዋል።
Read More...
የትምህርት ሴክተሩን ውጤታማ ለማድረግ የሙያ ብቃት ምዘናን በብቃት
  • በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ
የትምህርት ሴክተሩን ውጤታማ ለማድረግ የሙያ ብቃት ምዘናን በብቃት ያለፈና በስነ-ምግባር የታነጸ መምህርና የትምህርት አመራር እንዲኖር ለማድረግ ሰፊ ስራዎች እያከናወነ መሆኑን የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፍቃድ አሰጣጥና ዕድሳት ዳይሬክቶሬት የ2015 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና በቀጣይ ተግባራት ዙሪያ ከዞኖችና ከልዩ ወረዳዎች ከተወጣጡ የስራው አስተባባሪዎች ጋር ተወያይቷል፡፡
Read More...

General Information

AdministrativeLevel Region
Status Active

Organizations

Logo የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ
ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ የመጪው ትውልድ ቋንቋ ነው!!!
Type : መንግስታዊ
Logo በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ
Education for all
Type : መንግስታዊ
Logo በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የቴክኒክና ሙያ ት/ስልጠና ቢሮ
No Moto
Type : መንግስታዊ
Logo በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የብሄረሰቦች ም/ቤት
nomoto
Type : መንግስታዊ
Logo በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ
ee
Type : መንግስታዊ
Logo በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የፋይናንስ ቢሮ
nomoto
Type : መንግስታዊ
Logo በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ
Moto
Type : መንግስታዊ
Logo በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
Moto
Type : መንግስታዊ
Logo በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ባህልና ቱሪዝም ቢሮ
moto
Type : መንግስታዊ
Logo በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ
ፍትህ ለሁሉም!
Type : መንግስታዊ
Logo በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ
ከማምረት በላይ(beyond the product)
Type : መንግስታዊ
Logo በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ
nomoto
Type : መንግስታዊ
Logo በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
nomoto
Type : መንግስታዊ
Logo በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የክልል ም/ቤት ጽ/ቤት
nomoto
Type : መንግስታዊ
Logo በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
nomoto
Type : መንግስታዊ