Backtolist ጋሞ ዞን
1. አጠቃላይ የዞኑ ሁኔታ
1.1. የአመሰራረት ሁኔታ
የጋሞ ዞን በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ከሚገኙ ዞኖች አንዱ ነው፡፡
1.2. የህዝብ ብዛት(ወንድ፣ ሴት)
የዞኑ ህዝብ ብዛት 1,775,404
ነው፡፡
ከዚህም መሀል የወንድ 883,207 ሲሆን የሴት 892,197 ነው፡፡
1.3.
የዞኑ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ብዛት
ዞኑ በስሩ ሶስት ብሔሮችና ብሔረሰቦች ሲኖሩት እነዚህም ጋሞ፣ ዜይሴ እና ጊዲቾ ናቸው፡፡
1.4. የዞኑ አስተዳደር መቀመጫ ከተማ ስም
አርባምንጭ
1.5. የዞኑ የቆዳ ስፋት
የዞኑ የቆዳ ስፋት የውሀ አካላትን ጨምሮ 8013.7 ካሬ ኪ.ሜትር ነው፡፡
1.6.
የወረዳ ብዛት
14 ወረዳዎች
1.7.
የከተማ አስተዳደር ብዛት
6 ከተማ
አስተዳደሮች
1.8. የቀበሌ ብዛት
ዞኑ 296 ቀበሌያት አሉት፡፡
ዞኑ በ14 ወረዳዎች፣ በስድስት የከተማ አስተዳደሮች እና 296 ቀበሌያት የተዋቀረ ነው፡፡
2. የዞኑ የአየር ንብረት ሁኔታ
የዞኑ አየር ንብረቱ 28 በመቶ ደጋማ፣ 34 በመቶ ወይና ደጋማና 38 በመቶ ቆላማ ነው፡፡
ዞኑ ከ20-38°c የሙቀት መጠንና ከ200-2000 ሚሊ ሜትር አማካይ ዝናብ ያገኛል፡፡
3. ጂኦግራፊካል የመሬት አቀማመጡ
የዞኑ መልክዓ
ምድራዊ አቀማመጥ በኦሞና በስምጥ ሸለቆ መካከለ ተራራማ የሆነና በኢትዮጵያ ከሚገኙ ከፍታማ ቦታዎች መካከል የሚመደብ ነው፡፡
‘The Gamo Highlands’ ተብሎ የሚታወቅና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከፍታማ ቦታዎች የሚጠቃለል ነው፡፡ የዞኑ አዋሳኞች
በሰሜን ወላይታ ዞን፣ በደቡብ የሰገን አካባቢ ሕዝቦች ዞንና በደቡብ ኦሞ ዞን፣ በምስራቅ ጌዴኦ ዞን እና የሰገን አካባቢ ሕዝቦች
ዞንና፣ በምዕራብ ባስኬቶ ልዩ ወረዳ እንዲሁም ዳዉሮ ዞን ያዋስኑታል፡፡
የጋሞ ዞን
ቆዳ ስፋት የውሀ አካላትን ጨምሮ 8013.7 ካሬ ኪ.ሜትር የሚሰፋ ሲሆን ከ501-4207 ሜትረ ከባህር ጠለል በላይ ከፍታ ያለው ዞን ነው፡፡ ዞኑ
በ5°57’-6°71 N ላቲቲዩድ እና 36°37’-37°98’ E ሎንግትዩድ መስመሮች መካከል ይገኛል፡፡
ጠቅላላ መረጃዎች
የአስተዳደር አይነት | ዞን |
---|---|
ሁኔታ | አክቲቭ |