Backtolist የጉራጌ ዞን
አጠቃላይ የጉራጌ ዞን ገጽታ
ጉራጌ ዞን በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት
ካሉ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች አንዱ ሲሆን በሀገሪቱ በደቡብ አቅጣጫ ከአዲስ አበባ በ158ኪ/ሜ እና ከክልሉ ርዕሰ ከተማ ከሀዋሳ
በስተ ሠሜን 259ኪ/ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ዞኑ ከደቡብ ወደ ሰሜን ከ7.76-8.45 ላቲትዩድ እና ከምዕራብ ወደ ምስራቅ ከ37.46-38.71
ሎንግቲዩድ ላይ የሚገኝ ሲሆን አጎራባቾቹም በሰሜን በምስራቅ እና በምዕራብ ኦሮሚያ ክልል፣ በደቡብ ከሃድያና ስልጤ ዞኖችና በደቡብ
ምዕራብ ከየም ልዩ ወረዳ ናቸው፡፡ በዞኑ 8 ከተማ አስተዳደር እና 16 ወረዳዎች የሚገኙ ሲሆን በ412 የገጠር እና 49 የከተማ
ቀበሌዎች ተደራጅቷል፡፡ የዞኑ አስተዳደር መቀመጫ ወልቂጤ ከተማ ሲሆን በዞኑ ውስጥ በዋናነት የጉራጌ ፣ የቀቤናና ማረቆ ብሔረሰቦች
የሚኖሩ ሲሆን በተጨማሪ ሌሎች የሀገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦቸች ይኖራሉ፡፡ ዞኑ ከባህር ወለል በላይ ከ1,000 እስከ 3,700ሜትር
ከፍታ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የትላልቅ ተራሮች ባለቤት ነው ፤ከነዚህም ውስጥ ዘቢዳር 3,721ሜትር ፣አቦጋዴ 3,400 ሜትር እና
ጉንበር ናዳ 3,334 ሜትር ከፍታ ያላቸው ተራሮች ናቸው፡፡
ዞኑ በአራት ዋና ዋና የሥነ-ምህዳር ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን
4.1% ውርጭ፣27.5% ደጋ፣ 65.3% ወይና ደጋና 3.1% ቆላማ ስፍራዎችን ያካትታል፡፡ አማካይ አመታዊ የዝናብ መጠኑ ከ800
እስከ 1,400ሚ.ሜ እንደሚሆን ሲገመት ዓመታዊ አማካይ የሙቀት መጠኑ ደግሞ 18 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ይደርሳል፡፡ ዞኑ የተለያዩ
የግብርና ውጤት ሀብት ባለቤት ሲሆን በተለይ ጤፍ፣ በቆሎ፣ በርበሬ፣ እንሰት እና ጫት በብዛት እንደሚመረት ይታወቃል፡፡ እንዲሁም
የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማዕድናት እና ከፍተኛ የከርሰ-ምድርና የገጸ-ምድር ውሀ ባለሀብት ሲሆን ከታሪካዊ ቦታዎች እና ቅርስ አንፃር
በዩኔስኮ የተመዘገበው የጢያ ትክል ድንጋይ ጨምሮ የተለያዩ ገዳማት ታሪካዊ መስጂዶችና የጊቤ ተፋሰስ ፓርክ በውስጡ ይገኛሉ፡፡
የዞኑ የቆዳ ስፋት 5,893.4 ኪ.ካሜ ሲሆን
በሀገር አቀፍ የቤቶችና ህዝብ ቆጠራ ውጤት መሰረት የዞኑ ህዝብ ብዛት በ1999ዓ.ም 1,279,464 የነበረና
ከዚህ ውስጥ 622,078 (48.6%) ወንድ እና 657,568 (51.4%) ሴት ሲሆን በቆጠራ ትንበያ መሰረት
በ2013 ዓ.ም የህዝብ ብዛት 1,947,654 እንደደረሰ ሲገመት ከዚህ ውስጥ ወንድ 945,803(48.55%) እና ሴት 1001,851(51.45%) ይሸፍናሉ፡፡ የነዋሪው ህዝብ አሰፋፈር በአብዛኛው
በደጋ እና በወይን አደጋ ላይ ሲሆን ከጥግግት አንፃር በአንድ ካሬ ኪ/ሜትር 320.52 ሰዋች እንደሚኖሩ ይገመታል፡፡
ጠቅላላ መረጃዎች
የአስተዳደር አይነት | ዞን |
---|---|
ሁኔታ | አክቲቭ |