Backtolist ወላይታ ዞን

ወላይታ ዞን በክልሉ ካሉ ዞኖች አንዷ ትሆን ጂኦግራፊካል አቀማመጡ 6.51-7.35 ዲግሪ ሰሜን ላትቲውድ እና 37.23-38.14 ዲግሪ ምስራቃዊ ሎንግትዩድ መስመር ትገኛለች፡፡ ዞኑን ጋሞ ጎፋ ዞን በስተደቡብ፣ ዳውሮ ዞን በስተምዕራብ፤ ካምባታ ጣምባሮ ዞንና ሀዲያ ዞን ምዕራብ ባዳዋቾ ወረዳ በሰሜን፤ ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በስተሰሜናዊ ምስራቅ እና ሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በስተምስራቅ ያዋስናሉ፡፡ 

ዞኑ 16 የገጠር ወረዳዎች፤ 6 የከተማ አስተዳደር መዋቅሮች እና 372 ገጠርና ከተማ ቀበሌያት የተከፋፈለ ነው፡፡ ከዚህም 293 የገጠር እና 79 የከተማ ቀበሌያት ይገኙባታል፡፡ በዞኑ 6,664 የአ/አደር አደረጃጀት ልማት ቡድን፤ 42,322 የ1ለ5 አደረጃጀትና 349,224 አባላት፤ 9,558 የሴቶች አደረጃጀት ልማት ቡድን፤ 45,070 1ለ5 አደረጃጀትና 178,116 አባላት እና 2,199 የወጣቶች አደረጃጀት ልማት ቡድን፤ 12,379 1ለ5 አደረጃጀትና 185,687 አባላት መኖሩን መረጃ ይጠቁማል፡፡

የዞኑ ቆዳ ስፋት 451,170.7 ሄ/ር ወይም 4,511.7 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ነው፡፡ የዞኑ የመሬት አጠቃቀም ስልት በአብዛኛው ጥምር እርሻን የተከተለ የአስተራረስ ዘይቤ አለው፡፡ በአብዛኛው የእርሻ መሬት በዓመታዊና በቋሚ ሰብሎች የተያዘ ነው፡፡

የዞኑ የአየር ሁኔታ

ዞኑ የተለያየ የአየር ሁኔታ አለው፡፡ ከጠቅላላ ዞኑ ቆዳ ስፋት 157,909.5 (35%) ቆላ፣ 252,655.2 ሄ/ር (56%) ወይና ደጋ እና 40,605.3 ሄ/ር (9%) ደጋ የአየር ንብረት አለው፡፡ከዚህ የተነሳ የተለያዩ ሰብሎችን ለማምረት የተመቸ የአየር ጠባይ አለው፡፡ ዞኑ ከባህር ጠለል ያለው ከፍታ በዝቅተኛ 501 ሜትር በቢላቴ ጤና እና ከፍተኛ 2,958 ሜትር ዳሞታ ተራራ መሆኑን ነው፡፡ የዞኑ አማካይ ዓመታዊ የሙቀት መጠን 15.2-31.4 ዲግሪ ግሬድ ነው፡፡ ዓመታዊ የዝናብ መጠን በአማካይ ከ8ዐዐ-1,6ዐዐ ሚሜ ነው (ምንጭ፡ የክልሉ ፋይ/ኢ/ል/ቢሮ 2009 ዓ/ም ዓመታዊ አብስትራክት መረጃ መነሻ የወላይታ ዞን ፋይ/ኢ/ል/መምሪያ 2009 ዓ/ም ዓመታዊ አብስትራክት ዕትም)፡፡

በዞኑ አብዛኛው ሰብል ለማምረት የሚሆነው የዝናብ ውሃ ነው፡፡ ይሁንና ለመስኖ ምቹ የሆነ መሬት ያለው በመሆኑና ቋሚ ወንዞች ክረምት እስከ በጋ የማይደርቁ በመኖራቸው የዞኑ አ/አደር በባህላዊ እና በዘመናዊ ወንዞችን፤ ኩሬዎችን፤ የቤተሰብ ገንዳ እና የተለያዩ አነስተኛጥቃቅን የመስኖ አካላትን በመጠቀም እርሻውን ያለማል፡፡ በዞኑ የሚመረቱ ዋና ዋና ሰብሎችን በተመለከተ ቦቆሎ፤ ማሽላ፤ ጤፍ፤ ስንዴ፤ ገብስ፤ ቦሎቄ፤ አተር፤ ባቄላ፤ ጎደሬ፤ ስኳር ድንች፤ ድቡልቡል ድንች፤ ካሳቫ፤ እንሰት፤ አካዶ፤ ማንጎ፤ ሙዝ፤ ፓፓያ፤ ብርቱካን፤ አበሻ ጎመን፤ ቀይስር፤ ቲማቲም፤ ካሮት፤ ሽንኩርት፤ ቡና፤ ዝንጅብል በርበሬ እና ሌሎች ሰብሎችም ይመረታሉ፡፡

 የዞኑ አመሰራረት ሁኔታ

     ከሰሜን ኦሞ ክፍለ ሀገር በ1992 ዓ.ም ወላይታ ዞን በመባል ሰባት/7/ ወረዳዎችን ይዞ ተመሰረተ፡፡ እነሱም ሶዶ ወረዳ፤ሁምቦ ወረዳ፤ ዳሞት ጋሌ ወረዳ፤ ዳሞት ወይዴ ፤ኪንዶ ኮይሻ ፤ ቦሎሶ ሶሬ እና ኦፋ ወረዳ በመባል ተመስሪቷል፡፡




ወረዳዎች

...
ዳሞት ጋሌ
የአስተዳደር አይነት ወረዳ
...
የፍተሻ
የአስተዳደር አይነት ወረዳ
...
test wereda
የአስተዳደር አይነት ወረዳ

ጠቅላላ መረጃዎች

የአስተዳደር አይነት ዞን
ሁኔታ አክቲቭ

የሴክተር ተቋማት

Logo ስይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪራ
ህፍድስጅክፍድስፍጅ
አይነት : መንግስታዊ