Logo

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል

ደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ት ትንሿ ኢትዮጵያ

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥትን ከመሠረቱት አስር ክልሎች መካከል አንዱ ሲሆን በክልሉ የሚገኙ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በመከባበር፣ በመፈቃቀድና ዲሞክራሲያዊ አንድነታቸዉን በማጠናከር የጋራ ክልላቸዉን እየመሩና እያለሙ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የማንነታቸው መገለጫ የሆኑ ባህላዊና ታሪካዊ ዕሴቶች ያሏቸዉ ሲሆኑ፤ ዕሴቶቻቸዉን ለማስተዋወቅና ጥቅም ላይ ለማዋል የተደረገዉ ጥረት ዝቅተኛ ነዉ፡፡ በብሔረሰቦቹ ዙሪያ የተጻፉ ጽሑፎች አነስተኛ ብቻ ሳይሆኑ በመረጃ አጠቃቀምና በይዘታቸዉ ወጥነት የሚጎድላቸዉ ከመሆናቸዉም በላይ ባህላቸውንና ታሪካቸውን በጥልቀት ባልተረዱ የዉጪ ፀሐፍት የተጻፉ በመሆናቸዉ ክፍተቶች ተስተዉሎባቸዋል፡፡ በአገር ዉስጥ ምሁራን የተጻፉ ዉስን ሥራዎች ያሉ ቢሆኑም የእያንዳንዱን ብሄረሰብ ማንነት በተሟላ መልኩ የዳሰሱ አይደሉም፤ ለዚህም እንደ ምክንያት የሚገለጹት፡-
 

የክልሉ ብሔሮች፡ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ከደረሰባቸው ብሔራዊ ጭቆና በመላቀቅ፣ በአንድነት አብሮና ተሳስቦ ለመኖር፣ እንዲሁም የቃል ኪዳናቸዉ ማሰሪያ የሆነው ህገ-መንግሥት ያጐናፀፋቸውን ሰብአዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶቻቸውን በተሟላ ሁኔታ ለመጠቀም እንዲያስችላቸው ሕገ-መንግሥቱን በመቅረጽና በማጽደቅ በአዋጅ ቁጥር 1/1987 ዓ.ም መሠረት የጋራ ክልላቸውን መስርተዋል፡፡ በተሻሸለዉ የ1994 የክልሉ ህገ-መንግሥት አንቀጽ 48 መሰረት የብሄረሰቦች ምክር ቤት ተቋቁሞ የብሄረሰቦች የጋራ ተጠቃሚነት የሚረጋገጥበት፣ በማንነታቸዉ የሚታወቁበትና የሚኮሩበትን ሥርዓት ለመዘርጋት ጥረቱ የቀጠለ ሲሆን ከነዚህ ጥረቶች አንዱ የዚህ ፕሮፋይል ተዘጋጅቶ መቅረብ ነዉ፡፡
ኘሮፋይሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀዉ በ2001 ዓ.ም ሲሆን ለ2ኛ ጊዜም በ2004 ዓ.ም ታትሞ ስራ ላይ የዋለና ክልሉ አሁን የደረሰበትን የእድገት ደረጃ የሚያሳዩ መረጃዎችን በማካተት ለ3ተኛ ጊዜ ለማሳተም ተችሏል፡፡ በዚህ ፕሮፋይል ህትመት ዉስጥ ከዚህ ቀደም ሲል በታተሙት ዉስጥ እንደ ችግር የተመለከቱትን እጥረቶች ሙሉ በሙሉ ያስወግዳል ባይባልም እንደ ተከታታይ ሥራ በማገልገል ለቀጣይ ሥራዎች ጥሩ ሊባል የሚችል መነሻ እንደሚሆን ይገመታል፡፡ የኘሮፋይሉ ዋነኛ ዓላማም ብሔረሰቦቹ በመካከላቸዉ ያለውን ልዩነትና አንድነት በመረዳት እርስ በርስ እንዲተዋወቁ ልዩ የሚያደርጉአቸውን ጉዳዮች አውቀው፣ ተመሣሣይነትና ተወራራሽነት ያላቸውን ጉዳዮች እያጐለበቱ በመቻቻል አንድነታቸውን እንዲያጠናክሩ ለማስቻል ነው፡፡ ኘሮፋይሉ የባህል ፖሊሲውን በክልሉ ለመተግበር፣ የሕዝቦችን ትስስር በይበልጥ ለማጐልበት ብሎም በዘርፉ ጥናትና ምርምር ለሚያካሄዱ ዘርፎች አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡ የክልሉ ብሔረሰቦች በአብዛኛው የተፃፈ ታሪክ የሌላቸውና ያሉትም ቢሆኑ የተዛቡ በመሆናቸው ኘሮፋይሉን ለማዘጋጀት ዋነኛ የመረጃ ምንጭ ተደርገዉ የተወሰዱት በየደረጃው የሚገኙ መንግሥታዊ አስተዳደር እርከን መሪዎች፣ የየብሔረሰቡ ታዋቂ ሽማግሌዎችና ምሁራን ሲሆኑ ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ መረጃዎችን ከተለያዩ አግባብነት ካላቸው መንግሥታዊ ተቋማት ለመጠቀም ተሞክሯል፡፡ ጥናቱ ሙሉ በሙሉ ያለውን ጥሬ ሀቅ ከሀገር ሽማግሌዎች በመውሰድ ላይ የተመሠረተ ገለፃዊ አፃፃፍ ዘዴ (descriptive approach) የተከተለ ነው፡፡ የኘሮፋይሉ የመጀመሪያ ረቂቅ በየብሔረሰቦቹ አስተዳደር ተወካዮችናየ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን በተገኙበት ተተችቶ ማስተካከያዎች የተደረጉበት ሲሆን በዚህኛው ህትመት ላይ የማህበራዊና ኢኮኖማዊ መረጃዎች ለውጥ ብቻ ተደርገዋል፡፡

የኘሮፋይሉ አደረጃጀት የዞኖችንና ልዩ ወዳረዎችን አቀማመጥ የአማርኛ ፊደል ቅደም ተከተልን (Alphabetical order) መሠረት ያደረገ ሲሆን በአንድ ዞን ከአንድ በላይ ለሆኑ ብሔረሰቦች በብሔረሰቦቹ የአማርኛ ፊደል ቅደም ተከተል (Alphabet) መሠረት እንዲቀመጡ ተደርጓል፡፡

Source: snnprscon.info/

General Information

Distance Form Capital
0
Distance Form Parent
279
Capital City
Hawassa
Administration Level
Region
Status

List of Organizations | See all Organizations

Logo በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ
We will change the history of Ict in the region!

Type : Gov
8 Services
Logo በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ
No Moto

Type : Gov
0 Services
Logo በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የቴክኒክናሙያ ት/ስልጠናቢሮ
No Moto

Type : Gov
0 Services
Logo በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የብሄረሰቦች ም/ቤት
nomoto

Type : Gov
0 Services
Logo በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ
ee

Type : Gov
0 Services
Logo በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ
nomoto

Type : Gov
4 Services
Logo በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ከተማ ልማት ቢሮ
Moto

Type : Gov
0 Services
Logo በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የትራንስፖርትቢሮ
Moto

Type : Gov
0 Services
Logo በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ባህልና ቱሪዝም ቢሮ
moto

Type : Gov
0 Services
Logo በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ
ፍትህ ለሁሉም!

Type : Gov
0 Services